መንግሥት ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርሲቲያናት ምክር ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ ይሰራል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
መንግሥት ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርሲቲያናት ምክር ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ ይሰራል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፦ መንግሥት ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርሲቲያናት ምክር ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ አዲስ ከተመረጡት የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርሲቲያናት ምክር ቤት አመራሮች ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
የሃይማኖት አባቶች፣ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተከናወነው የምክር ቤቱ 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ መልኩ በመካሄዱ ለምክር ቤቱ አመራሮች አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።
መንግሥት ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርሲቲያናት ምክር ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ የሚሠራ ሲሆን በሚያስፈልገው ሁሉ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ለምክር ቤቱ አመራሮች መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸውም እመኛለሁ ነው ያሉት።