ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዎንታዊ ሚና ለመወጣት ሰፊ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል።
ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና የአረጋውያን ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ በበኩላቸው፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ አካታችና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡