ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት ሥራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት ሥራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋርተዋል
አዲስ አበባ፤የካቲት 1/2018 (ኢዜአ)፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ሥራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋርተዋል።
ዛሬ በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ እነዚህ ብርቱ ሰራተኞች በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች፤ በተለይም በካዛንቺስ የሕፃናት ዓለም፣ በስፖርት ፓርክ እና በአዲስ አኳሪየም ግንባታዎች፣ እንዲሁም ከኡራኤል እስከ ቦሌ ቪ.አይ.ፒ፣ ከኢንግሊዝ ኢምባሲ 22 እስከ ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል እና ከውኃ ልማት እስከ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ እየተከናወኑ ባሉ መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት አያያዥ መስመሮች ላይ ሌት ተቀን የሚተጉ ናቸው ብለዋል።
በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን፤ አዲስ አበባ ሁልጊዜም ታመሰግናችኋለች ሲሉም ገልፀዋል።
በከተማችሁ መልማት በመደሰት ሁሌ በማዕድ ማጋራት እና እነዚህን ብርቱ ሰራተኞ በማበረታት መርኃ ግብር እየተሳተፋችሁ ላላችሁ ባለሀብቶች በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች ፦
https://linktr.ee/ENADigital