ቀጥታ፡

ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ በሰቆጣ ከተማ ያስገነባው ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ተመረቀ

ሰቆጣ፤ የካቲት 1/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ በሰቆጣ ከተማ ያስገነባው ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ተመረቀ።

ቤተ-መጻሕፍቱን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መርቀውታል።


 

ቤተ-መጻሕፍቱ ትውልዱ በዕውቀትና በክህሎት ታጥቆ ለሀገር ግንባታ ሚናውን እንዲያጎላ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተመልክቷል።


 

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ፣ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም