አርሰናል ሰንደርላንድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ሰንደርላንድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አርሰናል ሰንደርላንድን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ዮኮሬስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ማርቲን ዙቢሜንዲ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ 17ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ56 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ዘጠኝ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሰንደርላንድ በ36 ነጥብ ከነበረበት 8ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ዝቅ ብሏል።
በሌሎች መርሐ-ግብሮች ቼልሲ ዎልቭስን 3 ለ 1፣ ዌስትሃም ዩናይትድ በርንሌይን 2 ለ 0 እና ፉልሃም ኤቨርተንን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
ቦርንማውዝ እና አስቶንቪላ አንድ አቻ ተለያይተዋል።