ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በብሔራዊ መግባባት የተመሰረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ወሳኝ ነው - የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በብሔራዊ መግባባት የተመሰረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል የምክክር አውድ ለመፍጠር በወሳኝ የምክክር ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

የምክክር ሂደቱም ዘላቂ ሀገራዊ ሰላምና ደኅንነትን በማጽናት ጠንካራ ሀገረ መንግስትና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየሰራ ነው።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዘላቂ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል ወሳኝ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ግዛቸው አይካ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ አካታችና አሰባሳቢ ሀገራዊ ምክክር በዜጎች መካከል የሚስተዋሉ አለመግባባቶችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

የምክክር ሂደቱም በሰለጠነ የጠረጴዛ ላይ የምክክር ሥርዓት የቆዩ ሀገራዊ ቅራዎችን በአዲስ የምክክር ምዕራፍ ዘላቂ እልባት ለመስጠት በድልድይነት የሚያገለግል መሆኑን ተናግረዋል።


 

ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ሀገረ ለማስተላለፍ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል ምክክርን መከተል ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ ሌላኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል አቶ መስፍን መንግስቱ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክርም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰለጠነ ምክክር በማካሄድ ጠንካራ ሀገረ መንግስትን ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሀገራዊ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም