ቀጥታ፡

ሰራዊቱ ለሀገሩ ክብርና ለዜጎች ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጀግንነት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው- ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ

ሰቆጣ፤ ጥር 30/2018(ኢዜአ)፡- ሰራዊቱ ለሀገሩ ክብርና ለዜጎች ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጀግንነት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ ገለጹ።

የእዙ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የፓናል ውይይት በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል።


 

በመደረኩ ላይ የተገኙት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ፤ የኢትዮጵያን ክብርና ሉአላዊነት በአስተማማኝ መልኩ የሚያስከብር ጠንካራ ሰራዊት መገንባቱን ገልጸዋል። 

በመሆኑም ሰራዊቱ ለሀገሩ ክብርና ለዜጎች ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጀግንነት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የባእዳንን ተልእኮ ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ ባንዳዎችን ተከታትሎ እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም ለሰላም አማራጭ ዝግጁ የሆኑትን በመቀበል በተለይም በአማራ ክልል የሰላም ማስከበር ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

በቀጣይም ከውስጥ ባንዳዎችና ከባእዳን ለሚሞከሩ ማናቸውም የጥፋት እንቅስቃሴዎች የሰራዊቱ ፈጣን ምላሽና የወትሮ ዝግጁነት የተሟላ ነው ብለዋል።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጌትነት እሸቱ፤ የዳሎል ማዕከላዊ እዝ የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ በክልሉ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም