ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ አራተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 0 አሸንፏል። 

በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብራያን ምቡዌሞ በ38ኛው እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ81ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

የቶተንሃም ሆትስፐርሱ ተከላካይ ክርስቲያን ሮሜሮ በ29ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

የተጫዋቹ መውጣት በቶተንሃም የጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል። 

በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ዩናይትድ በ44 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ 12ኛ ድሉን አስመዝግቧል። 

በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ29 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም