ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የክልል እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቶች፣ የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ አባላትና የሥራ አስፈፃሚዎች፣ ታዋቂ ዑለሞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


 

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ የሰነድ ርክክብ ተከናውኗል።

በተጨማሪም በጉባኤው የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት እንዲሁም የሥራ አስፈፃሚ ማሟያ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።


 

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ጉባኤው መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ምርጫችን በመስጅዳችን በሚል መሪ ሐሳብ ወኪሎቹን በመረጠበት ማግስት የተካሄደ በመሆኑ ታሪካዊ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም