ቀጥታ፡

ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክር ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2018(ኢዜአ)፦ ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጸህፈት ቤት ገለጸ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ውጥን የተገነባው እና በ13.3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት መርቀዋል።


 

ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሁሉንም ዓይነት መገልገያዎች አሟልቶ የያዘ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

ሪዞርቱ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምግብ ቤቶችን፣ የመዋኛ ገንዳዎችን፣ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶችን እና የሄሊኮፕተር ማረፊያን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት መገልገያዎች አሟልቶ መያዙን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። 

በተጨማሪም በተለያዩ የፍራፍሬ ዞኖች እና ለዓይን በሚማርኩ አረንጓዴ ስፍራዎች የታጀበ በመሆኑ፤ ለጎብኚዎች የማይረሳ ትውስታን የሚሰጥ እጅግ ማራኪ ቦታ መሆኑንም ገልጿል።




‎ይህ ሪዞርት ከያዛቸው ዘመናዊ መገልገያዎች ባሻገር፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክር መሆኑንም እንዲሁ። 

የቱሪዝም ልማቱን ከተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ፣ ከዘላቂነት እና ከአካታችነት ጋር በማቀናጀት፤ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ጥልቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ እሴት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅበት ሰፊ ገበታ ሆኖ ያገለግላል ነው ያለው ጽህፈት ቤቱ።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም