ሊድስ ዩናይትድ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል - ኢዜአ አማርኛ
ሊድስ ዩናይትድ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ-ግብር ሊድስ ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጄይደን ቦግል፣ ኖህ ኦካፎር እና ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘው አጥቂው
ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን በዘንድሮው የውድድር ዓመት 10ኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሎሬንዞ ሉካ ለፎረስት ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ላይ ሊድስ ዩናይትድ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።
ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሊድስ ዩናይትድ በ29 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱም ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
ላለመውረድ በሚደረገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኖቲንግሃም ፎረስት በ26 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።
ባለፉት ሁለት የሊጉ ጨዋታዎች ያላሸነፈው
ኖቲንግሃም ፎረስት የወራጅ ቀጠና ስጋት ውስጥ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት እስከ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።