ቀጥታ፡

አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ32ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል አርባምንጭ ከተማ መሪ ሆኗል።

በ38ኛው ደቂቃ አቤል ነጋሽ የድሬዳዋ ከተማን የአቻነት ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ12 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዞ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቋል።  ቡድኑ በውድድር ዓመቱ ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም