ቀጥታ፡

መዲናዋን የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ለኩነቶች መጨመር አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡- አዲስ አበባን የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ በርካታ የልማት ስራዎችና ሜጋ ፕሮጀክቶች ፍሬ በማፍራት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ኩነቶች እንዲጨምሩ ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን በመኬሄድ ላይ ነው።


 

በጉባኤው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ለምክር ቤቱ በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

በዚህም የቱሪዝም ዘርፉን አፈጻጸም አስመልክቶ ባለፉት ስድስት ወራት 150 የሚሆኑ አሕጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኩነቶች በአዲስ አበባ መካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም ነው የጠቀሱት፡፡


 

አዲስ አበባን የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ለኩነቶች መጨመር በተጨባጭ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

በአጠቃላይ ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ከውጭ ሀገር የቱሪስት ፍሰት ባለፉት ስድስት ወራት 155 ቢሊየን ብር ወደ ኢኮኖሚው ፈሰስ ተደርጓል ብለዋል፡፡

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም