ቄስ ደረጄ ጀንበሩ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ ተመረጡ - ኢዜአ አማርኛ
ቄስ ደረጄ ጀንበሩ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ ተመረጡ
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ቄስ ደረጄ ጀንበሩ ለቀጣዩ አምስት ዓመታት የካውንስሉ ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ መረጠ።
በዛሬው እለት በተደረገው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በካውንስሉ ውስጥ በቀጣዩ አምስት ዓመታት በአመራርነት የሚያገለግሉ መሪዎች ተመርጠዋል።
በዚህም ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት በመሆን ያገለገሉትን ዶክተር ጣሰው ገብሬን በመተካት ቄስ ደረጄ ጀንበሩ ለቀጣዩ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።
ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ምክትል ፕሬዚደንት በመሆን ያገለገሉትን ሐዋሪያ ዮሐንስ ግርማን በመተካትም መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ እና በድጋሚ ዶክተር ቤተ መንግስቱ ለቀጣዩ አምስት አመታት የካውንስሉ ምክትል ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።
ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሓፊ የነበሩትን ቄስ ደረጄ ጀንበሩን በመወከል ፓስተር ዶክተር ጌትነት ለማ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ በመሆን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ለተመረጡት መሪዎች መልካም የስራ ዘመንን መመኘቱን ከካውንስሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።