ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና የተመድ የቱሪዝም ድርጅት ኢትዮጵያ ኢኮ ቱሪዝምን ለማስፋት እያከናወነችው ባለው ተግባራት ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት(UN Tourism) ዋና ፀሐፊ ሸይካ አል ኖዊስ ጋር ኢትዮጵያ ኢኮ ቱሪዝምን ለማስፋት እያከናወነችው ባለው ተግባራት ዙሪያ መክረዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋት እያከናወነች ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ሸይካ አል ኖዊስ ገልጸዋል።


 

ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ድርጅቱ በአቅም ግንባታ፣ ዘላቂ በሆኑ ኢንሼቲቮችና የፋይናንስ ሀብት አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።

ዋና ፀሐፊዋ ኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃን ከግምት በማስገባት የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋትና ለማሳደግ እያከናወነች ያለውን ስራ ማድነቃቸውን ኢዜአ ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራ ልዑክ በዱባይ እየተካሄደ ባለው የ2026 የዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም