ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢነት ሹመት አጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ለኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባልነት በዕጩነት የቀረቡለትን ግለሰቦች መርምሮ አጽድቋል።
በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እንደገና ለማቋቋም በ2015 የወጣው አዋጅ፤ የተቋሙ የስራ አመራር ቦርድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ ይደነግጋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ረዳት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ የኮርፖሬሽኑን የስራ አመራር ቦርድ አባላትን የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የኮርፖሬሽኑ ቦርድ፤ የብሔራዊ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያዎችን በስሩ የሚያስተዳድረውን ኢቢሲን በበላይነት የሚመራ ተቋም በመሆኑ የሀገሪቱን ወቅታዊና ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ የስራ ቦርድ አባላት እንደሚፈልግ ገልጸዋል።
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጽሑፎቻቸው፣ በታሪክ ተመራማሪነታቸውና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ባላቸው ንቁ ተሳትፎ የሚታወቁ እና በተለያዩ ተቋማት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ማገልገላቸውን ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ ለኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባልነት የቀረቡ ዘጠኝ ዕጩዎችን ሹመት አፅድቋል።
በዚህም፦
1- ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የቦርዱ ሰብሳቢ
2- ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) - አባል
3- ዶክተር መቅደስ ዳባ - አባል
4- እንደገና አበበ(ዶ/ር) - አባል
5- አቶ ቸሩጌታ ገነነ - አባል
6- ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) - አባል
7- አቶ ጃፋር በድሩ - ከዚህ በፊት አባል የነበሩ
8- አቶ የሱፍ ኢብራሂም - ከዚህ በፊት አባል የነበሩ
9- አብዱልዋሳ አብዱላሂ(ዶ/ር) - ከዚህ በፊት አባል የነበሩ በአባልነታቸው እንዲቀጥሉ ተደርጓል።