የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀመረ
ሻኪሶ፤ ጥር 28/2018 (ኢዜአ) ፡-የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ በ124 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ መሆኑ ተጠቁሟል።
በይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል፣ የክልልና የጉጂ ዞን አመራሮችና አባ ገዳዎች ተገኝተዋል።