ማንችስተር ሲቲ ለካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ለካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018(ኢዜአ)፦ በካራባኦ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦማር ማርሙሽ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቲጃኒ ራያንደርስ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝቷል።
አንቶኒ ኢላንጋ ለኒውካስትል ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
በጨዋታው ላይ ማንችስተር ሲቲ በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስዶ ቢጫወትም የግብ እድሎችን በመፍጠር ረገድ ቡድኖቹ ተመጣጣኝ ነበሩ።
የሲቲው አጥቂ ኦማር ማርሙሽ የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በአጠቃላይ ድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ለካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ አልፏል።
የስምንት ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ማንችስተር ሲቲ በፍጻሜው ከሁለት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ አርሰናል ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።
የፍጻሜው ጨዋታ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።
የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ኒውካስትል ዩናይትድ የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞ ግማሽ ፍጻሜ ላይ ተገትቷል።