ሃዋሳ ከተማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በ7ኛው እና ተባረክ ሄፋሞ በ14ኛው ደቂቃ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ጋር በነጥብ እኩል ቢሆንም የግብ ክፍያ ብልጫ ተወስዶበታል።
ሃዋሳ ከተማ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ28 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
በተያያዘም ዛሬ በተደረጉ የ18ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።
ሀዲያ ሆሳዕና እና መቻል አንድ አቻ ሲወጡ ሸገር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።