በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማስቀጠል የድርሻችንን እንወጣለን - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማስቀጠል የድርሻችንን እንወጣለን
ወልዲያ ፤ ጥር 27/2018(ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የመንግስትን የ2018 በጀት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም መንግስታቸው፣ ባለፉት ስድስት ወራት በማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ያከናወናቸው ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን አብራርተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራሪያ አስመልክቶ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የህዝብን የሰላምና ልማት ጥያዌዎች ለመመለስ ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል።
ይህንንም በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማስቀጠልም የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።
አስተያየታቸወን ከሰጡ የወልዲያ ነዋሪዎቸ መካከል ይድነቃቸው ለገሰ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኛ አመራር በኢትዮጵያ የሚታይ ዕድገት መምጣቱን ገልጸዋል።
በኮሪደር ልማት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋትና በሌሎችም የልማት መስኮች እየታየ ያለው ውጤት ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
በኢንዱስትሪና በማዕድን ዘርፉ እየታየ ያለው ዕድገት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እየፈጠረ ነው ብለዋል።
እንደ ሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ የተጀመሩ የልማትና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
መንግስት የጀመራቸው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የኢትዮጰያን መጻዒ ዕጣ ፈንታ የተሻለ ለማድረግ ቁልፍ ሚና አንዳላቸው የተናገሩት ደግሞ በላይ ገላው ናቸው።
ቀደም ሲል ትኩረት ተነፍጎት የቆየው የቱሪዝም ዘርፍን ጨምሮ በግብርና ምርትና ምርታማነት ላይ እየታየ ያለው ለውጥ የመንግስትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
አሁን በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊ ልማት ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ ሰላምና ልማት ዘብ ሊቆም አንደሚገባ አመልክተዋል።
መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያን በመገንባት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቀው ደግሞ ወጣት አበበ አለማየሁ ነው።
ወጣቶች የዲጂታል ክህሎታቸውን በማሳደግ በሀገር ወስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸው ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሷል።
ወጣቶች በየአካበቢያቸው የሚፈጠሩ ጥቃቅን ቸግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለአገራቸው የልማትና የቴክኖሎጂ ዕድገት የድርሻቸውን በመወጣት ከመንግስት ጎን መቆም ይገባል ብሏል።