ሀዲያ ሆሳዕና እና መቻል አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሀዲያ ሆሳዕና እና መቻል አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና እና መቻል ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ መቻል መሪ ሆኗል።
ደስታ ዋሚሾ በ32ኛው ደቂቃ ለሀዲያ ሆሳዕና የአቻነቷን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ሀዲያ ሆሳዕና በ21 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል። ክለቡ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
መቻል በ30 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
በአሁኑ ሰዓት አዳማ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።