ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥብ ጣለ  

አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተደርጓል።


 

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 35 ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ሃዋሳ ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ያገኘውን እድል አልተጠቀመም።

ሲዳማ ቡና ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ27 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። 

ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ላይ ድል አልቀናውም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም