ቀጥታ፡

ታዋቂው የገዳ ሥርዓት ተመራማሪ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018 (ኢዜአ)፦ታዋቂው የገዳ ስርዓት ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ፕሮፌሰር አስመሮም የገዳ ሥርዓት እንዲጠበቅ፣ እንዲከበርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ የሰሩ ነበሩ።

በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ እሴቶችና የሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆዎች በጽሑፍ ተመዝግበው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በገዳ ሥርዓት ዙሪያ በርካታ መጻሕፍትና የምርምር ሥራዎችን ለንባብ ያበቁት ፕሮፌሰሩ የሥርዓቱን ዴሞክራሲያዊነት በማጉላት ለሰብአዊ መብት መከበርና ለሕዝቦች ክብር በጽናት የታገሉም ሰው ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በአስመሮም ለገሰ (ፕ/ር) ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም