ሸገር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሸገር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው የተካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ21 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ተከታታይ ድል ማስመዝገብ አልቻለም።
ምድረ ገነት ሽሬ በ23 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።