ቀጥታ፡

በኦስትራቫ በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው 

አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ትናንት ማምሻውን በቼክ ሪፐብሊክ ኦስትራቫ ተካሂዷል።

በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ብርቄ ኃየሎም 4 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ ከ62 ማይክሮ ሰከንድ አሸንፋለች። በ2026 በርቀቱ የዓለም ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች።

ሳሮን በርሄ 4 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ ከ23 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ፣ ሀገረወይን ካላዩ 4 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ ከ92 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ሁለቱም አትሌቶች በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓታቸውን አስመዝግበዋል።

ፅጌ ተሾመ 8ኛ እና አክሱማዊት አምባዬ 12ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።


 

 በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት ንግስት ጌታቸው 1 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ከ98 ማይክሮ ሰከንድ አሸንፋለች።

በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች ኤርሚያስ ግርማ አራተኛ፣ ሚልኬሳ ፍቃዱ ሰባተኛ እና ወገኔ አዲሱ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል።

ፖርቹጋላዊው ኢሳቅ ናደር ፣ ደቡብ አፍሪካዊው ሼፖ ሺቴ  እና ቤልጂየማዊው ጆን ሄይማንስ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም