ማንችስተር ሲቲ ከኒውካስትል ዩናይትድ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ከኒውካስትል ዩናይትድ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ የሁለተኛ ዙር መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ይጫወታሉ።
ጨዋታው ምሽት አምስት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ይከናወናል።
ሁለቱ ክለቦች ጥር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ 2 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።
ማንችስተር ሲቲ የካራባኦ ዋንጫን ስምንት ጊዜ በማንሳት ከሊቨርፑል (10) ቀጥሎ ስኬታማው ክለብ ነው።
ኒውካስትል ዩናይትድ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ነው።
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በካራባኦ ዋንጫ ሁለት ጊዜ ተገናኝተው በተመሳሳይ አንድ አንድ ጊዜ አሸንፈዋል።
ማንችስተር ሲቲ ለፍጻሜ ለማለፍ ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት በቂው ነው።
ኒውካስትል ዩናይትድ የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ ከባድ ፈተና ከፊቱ ተጋርጦበታል።
ኒውካስትል ከሁለት እና ከዚህ በላይ የግብ ልዩነት ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ ይኖርበታል።
ቶኒ ሀሪንግተን ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በፍጻሜው አርሰናል ጋር ይገናኛል።
አርሰናል ትናንት ከቼልሲ ጋር ባደረገው የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ በአጠቃላይ ድምር ውጤት ተጋጣሚውን 4 ለ 2 በመርታት ለፍጻሜ አልፏል።