የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018 (ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አድርጓል።
ካቢኔው በከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን ማሳለፉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሁናዊ የከተማዋ ፈጣን ዕድገት እና ለውጥ መሰረት ያደረገ በአምስት ዋና ደረጃዎች እና በሰላሳ ንኡሳን ደረጃዎች የቦታ ደረጃ (Land grading) ጥናት ቀርቦ፣ በቀረበው ደረጃ መሰረት የተሻሻለ የሊዝ መነሻ ዋጋ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
የከተማዋን የግዢን እና ንብረት አስተዳደር ሂደት እና ስርዓት ለማዘመን፣ የስራ ቅልጥፍናን ለማላቅ እንዲሁም ንብረትን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ” ላይም ተወያይቶ እንዲፀድቅ ለምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል።
በተጨማሪም ካቢኔው ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ምደባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።