በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊየን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን እየሠራን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊየን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን እየሠራን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018(ኢዜአ)፦ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊየን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን እየሠራን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊየን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን እየሠራን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ እቅድ ግዙፍ ቢመስልም፣ ካለን የቤት ፍላጎት አንጻር ሲታይ ግን ገና አነስተኛ ነው ብለዋል።