ቀጥታ፡

የትምህርት ሥርዓቱን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያስገኙ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ሥርዓቱን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በተገኙበት 5 ዓመት የሥራ ዘመን 10 መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በፌዴራል መንግሥት 2018 በጀት ዓመት 6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ባለፉት ዓመታት የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት ለማሻሻል በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ግልጽ የሆነ ፍኖተ ካርታ ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱንና ውጤታማ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ለማስፋፋት በርካታ የመሠረተ ልማት ግንባታ መከናወናቸውን ጠቁመው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች 34 ሺህ በላይ የመዋዕለ ሕፃናት መገንባታቸውን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከአራት ሚሊዮን በላይ ሕፃናት በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ትምህርት እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ከመሠረተ ልማት ማሻሻያ ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለሚያረጋግጡ ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል ብለዋል፡፡

የመምህራን ሥልጠና፣ የምዘና ሂደትን ማዘመንና ቴክኖሎጂን መጠቀም በትምህርት ዘርፉ ለውጥ እንደሚያመጡ ታምኖባቸው እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለታዳጊዎች ዕውቀት በሰጠችው ትኩረት ነገን እየሠራች ትገኛለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋ ሕፃናት በመሆናቸው፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ የታነጹና የተዘጋጁ ሕፃናት በነገው ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ ሲሉም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም