የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018 (ኢዜአ)፦የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተያያዘ በሰጡት ማብራርያ÷ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት አሁን ላይ 33 ማዕከላት ማድረስ እንደተቻለ ገልጸዋል።
በቀጣይም የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ዜጎች የመንግስትን አገልግሎት በተሻለ ጥራት እንዲያገኙ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የተጀመረበት ጊዜ አጭር ቢሆንም በዘርፉ ላይ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ አስገንዝበዋል።
የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጠት መጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
በባሶች በመንቀሳቀስ ጭምር በተለዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ የኦን ላይን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትም የዜጎችን የመንግስት አገልግሎት ጥራትና ደረጃ በማሻሻል እንግልትን እየቀነሰ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።