ቀጥታ፡

የአፍሪካ ቀንድ እንዳይቀደድ የተሰፋ፤ እንዳይጣመር የተቀፈደደ ከባቢ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ጥር 26 /2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካ ቀንድ እንዳይቀደድ የተሰፋ፤ እንዳይጣመር የተቀፈደደ ከባቢ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ከባቢን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ የአፍሪካ ቀንድ እንዳይቀደድ የተሰፋ፤ እንዳይጣመር የተቀፈደደ ከባቢ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፥ በባህልና ቀንቋ የሚተሳሰሩ ህዝቦች ያሉበት ቢሆንም ከፍተኛ ፉክክርና ጣልቃ ገብነት ያለው ከባቢ ነው ያሉት።

የሁለቱ ውሃዎች ጉዳይ እኛንም እያተረማመሰ በእኛ ጉዳይ የሚገቡ ሃይሎችን እያሰፋ አንዱ ለአንዱ መከታ ሊሆን ሲገባው ችግር አስተላላፊ መሆኑን ገልጸው፥ በዚህ ምክንያት ቀጠናው የራሱ ችግር ያለበት በመሆኑ ይህን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፤እንደሚሳካም እምነት አለኝ ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም