ቀጥታ፡

መንግስት ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ አካታች እንዲሁም ካለፈው በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክሮ እየሰራ ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ጥር 26 /2018 (ኢዜአ)፦መንግስት ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ አካታች እንዲሁም ካለፈው በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ምርጫን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ መንግስት ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ አካታች እንዲሁም ባለፈው ምርጫ በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክሮ እየሰራ ነው ብለዋል።

ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከባለፈው የተሻለ እንደሚሆን በውጤቱ መመልከት እንደሚገባ አመልክተዋል።

ፓርላማው ብዝሃ ድምጽ ሊኖረው ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ምርጫው ምክር ቤቱ ልዩ ድምጾች የሚሰሙበት አውድ ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ፓርማላው የአንድ ፓርቲ ድምጽ ከሆነ ለኢትዮጵያ እንደማይጠቅማት ጠቅሰው፥ ይህ እንዲቀየር እና በርካታ ድምጾች እንዲሰሙ መንግስት በትጋት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ልዩ ድምጾች ለመንግስት አልፎም ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም