በኢኮኖሚ፣ በተቋማት ግንባታ የማድረግ አቅማችንን የምናሳድገው ኢትዮጵያን የሚያጸኑ ምሰሶዎችን መጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በኢኮኖሚ፣ በተቋማት ግንባታ የማድረግ አቅማችንን የምናሳድገው ኢትዮጵያን የሚያጸኑ ምሰሶዎችን መጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢኮኖሚ፣ በተቋማት ግንባታ የማድረግ አቅማችንን የምናሳድገው ኢትዮጵያን የሚያጸኑ ምሰሶዎችን መጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
በማብራሪያቸውም በኢኮኖሚ፣ በተቋማት ግንባታ የማድረግ አቅማችንን የምናሳድገው ኢትዮጵያን የሚያጸኑ ምሰሶዎችን መጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ነው ብለዋል።
ለአብነትም የኢትዮጵያ አየር ሃይል በለውጡ ማግስት አንድ ሄሌኮፕተር ብቻ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ የተለያዩ ስምና ተግባር ያላቸው ከ100 በላይ አውሮፕላኖችን ታጥቋል። ይህ የተቋም ግንባታ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
አሁንም ቢሆን ሀገር ከመጠበቅ ጎን ለጎን የትኛውም የውስጥ ሃይል ወደ ሰላማዊ መንገድ ሲመለስ ለይቅርታ ዝግጁ መሆን አለብን ጉዳያችን ኢትዮጵያ ብቻ መሆን አለበት ነው ያሉት በማብራሪያቸው።