ቀጥታ፡

ወጣቶችን ለነገ ውድድር ከወዲሁ ማዘጋጀት ያስፈልጋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018(ኢዜአ)፦ ወጣቶችን ለነገ ውድድር ከወዲሁ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወጣቶችን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

በማብራሪያቸውም ወጣቶችን ለነገ ውድድር ከወዲሁ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል።

ከዚህ አንጻር ከኢትዮጵያ አምስቱ የእደገት ምሶሶዎች አንደኛው ቴክኖሎጂ እንዲሆን በማድረግ ለትውልድ ሲሰራ ቆይቷል ነው ያሉት።

ኤአይ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።

በኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛ የሆነውን የኤአይ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥለው አንድ ዓመት ውስጥ ስራ ይጀምራል ብለዋል።

ይህ ዩኒቨርሲቲ አባቶቻችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ገንብተው ስመጥር እንዳደረጉት ሁሉ ለልጆቻችን ለነገ የተሻለ ዘመን ይዞ ይመጣል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም