ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ፤ ጥር 25/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።

በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት በ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም