ቀጥታ፡

የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት የሚጥሩ ፋብሪካዎች ሀገራዊ አበርክቷቸው ቀላል አይደለም-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት የሚጥሩ ፋብሪካዎች ሀገራዊ አበርክቷቸው ቀላል የሚባል አይደለም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ።



ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን አማጋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።



በቅርቡ ወደ ሥራ የገባው ፋብሪካው፤ ተከላው ሙሉ በሙሉ በቅርቡ ሲጠናቀቅ በዋናነት ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ፣ የሶፋ ልብስ፣ መጋረጃ፣ የአንሶላ ጨርቅ፣ ጂንስ እና ሁሉንም አይነት የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች በተለየዩ ዲዛይኖች እና ልኬት ማምረት ያስችለዋል ብለዋል።



ጥራት ያላቸው ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱና በቀጥታ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ፤ የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት የሚጥሩ ፋብሪካዎች ሀገራዊ አበርክቷቸው ቀላል የሚባል አይደለም ሲሉም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም