ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፡- በ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 ረትቷል።


 

10 ሠዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ፋሲል ከነማ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቶሎሳ ንጉሴ በራስ ላይ ባስቆጠራት ግብ አሸናፊ ሆኗል።

ቀደም ብሎ 9 ሠዓት ላይ በተካሄደው የዕለቱ መርሐ-ግብር መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወቃል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም