መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፡- በ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተገናኙት መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።
በጨዋታው ላይ የኢትዮጵያ ቡናው ራምኬል ጀምስ በ19ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናን መሪ ያደረች ግብ ማስቆጠር ችሏል።
እንዲሁም በ31ኛው ደቂቃ በፍቃዱ ዓለማየሁ (በራስ ላይ) ግብ በማስቆጠሩ ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ አቻ የወጣበትን ዕድል አግኝቷል።