ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐርን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐርን አግኝቼ በቁልፍ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።


 

‎ከውይይታቸው ጎን ለጎን በተካሄደው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ማእቀፍ ሥር የኢንቨስትመንት እና ኃብት አስተዳደር የቴክኒካል ትብብር የመግባቢያ ሥምምነት እና የሁለት የጋራ የልማት ስምምነቶች ፊርማ መርሃ ግብር ላይም ተገኝተናል ነው ያሉት።

እነዚህም የሁርሶ-አይሻ 400 ኪሎ ቮልት እና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ስምምነቶች ናቸው ብለዋል።


 

እነዚህ ስምምነቶች ትብብርን በማጠናከር እና ስትራቴጂያዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ርምጃን የሚያሳዩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም