አርባምንጭ ከተማ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
አርባምንጭ ከተማ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አርባምንጭ ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥሯል።
ፍሬው ሰለሞን ለወልዋሎ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው አርባምንጭ ከተማ በ11 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ16 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።