ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት የዱባይ ማራቶን - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት የዱባይ ማራቶን
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ ዛሬ ማለዳ በተካሄደው 25ኛው የዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል።
በወንዶች አትሌት ንብረት መላክ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ አንደኛ ወጥቷል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ያሲን ሃጂ ሁለተኛ እና ሩዋንዳዊው ጆን ሃኪዚማና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ4ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶች አንቺንአሉ ደሴ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ አሸንፋለች።
ሙሉዬ ደቀቦ እና ፋንቱ ወርቁ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ 10ኛ ደረጃን በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።
በሁለቱም ጾታዎች ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተመሳሳይ የ80 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የውድድሩ አዘጋጅ አካል በአጠቃላይ ለአትሌቶች ከ336 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ሽልማት መስጠቱን አስታውቋል።
እ.አ.አ በ1998 የተጀመረው የዱባይ ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ የተሰጠው የጎዳና ላይ ውድድር ነው።