በሊጉ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከማንችስተር ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድ ከፉልሃም የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከማንችስተር ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድ ከፉልሃም የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከማንችስተር ሲቲ በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ28 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ በ46 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
ተጋጣሚው ማንችስተር ሲቲ የዛሬው ጨዋታ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ እና ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ ለማድረግ ያስችለዋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታውን በኦልትራፎርድ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በ38 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ፉልሃም በ34 ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
በጊዚያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ እየተመራ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች የሊጉን መሪ አርሰናል እና ተከታዩን ማንችስተር ሲቲ ያሸነፈው ዩናይትድ በጥሩ መነቃቃት ላይ ይገኛል።
የዛሬውንም ጨዋታ የማሸነፍ ግምት አግኝቷል። ሶስት ነጥብ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ነው።
በ23 ሳምንት ብራይተንን ያሸነፈው ተጋጣሚው ፉልሃም ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።
በቪላ ፓርክ ስታዲየም አስቶንቪላ ከብሬንትፎርድ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
አስቶንቪላ በ46 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ብሬንትፎርድ በ33 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ማሸነፍ አስቶንቪላን በዋንጫ ፉክክሩ ላይ እንዲቆይ ያደርገዋል። ተጋጣሚው ብሬንትፎርድ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
ኖቲንግሃም ፎረስት ከክሪስታል ፓላስ ከቀኑ 11 ሰዓት በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ይጫወታሉ።