ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ሊቨርፑል ኒውካስትል ዩናይትድን 4 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሁጎ ኢኪቲኬ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፍሎሪያን ዊትዝ እና ኢብራሂማ ኮናቴ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ኢኪቲኬ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
በቅርቡ አባቱን በሞት ያጣው ኢብራሂማ ኮናቴ ግብ ካስቆጠረ በኋላ በእንባ ስሜቱን ገልጿል።
አንቶኒ ጎርደን ለኒውካስትል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከአምስቱ የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሊቨርፑል በ39 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቀያዮቹ እ.አ.አ በ2026 የመጀመሪያ የሊግ ድላቸውን አግኝተዋል።
ሊቨርፑል በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በሊጉ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኒውካስትል ዩናይትድ በ33 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።