ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድኑር ናስር በ64ኛው እና በ71ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ድሬዳዋ ከተማ በ23 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለሰባተኛ ጊዜ የተሸነፈው ሀድያ ሆሳዕና በ20 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል።