ቀጥታ፡

የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ ተመረቀ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ፤ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት ማስመዝገቧን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት እንደገለጸው ኢትዮጵያ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ፤ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት አስመዝግባለች።

ይህ ውጤት የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችንን ለማስፋፋት የወሰድነው ወሳኝ እርምጃ ምልክት ነው ሲሉም አስታውቋል።

የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት በቴክኖሎጂ ለሚመራ ኢኮኖሚ ዋነኛው የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን፤ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ያላትን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ ብቻ ሳትሆን ከፍ ያሉ ርዕዮቿን ለመፈፀም በቂ አቅም ያላት መሆኑንም በተግባር አሳይቷል ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም