ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ  አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም በ41ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ወላይታ ድቻ መሪ ሆኗል።

ከእረፍት መልስ አቤነዘር ሲሳይ በ69ኛው የአዳማ ከተማን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ16 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

አዳማ ከተማ በ28 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል።

ዛሬ በተጀመረው 18ኛ ሳምንት ቀን ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ሃዋሳ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ምድረ ገነት ሽሬ እና ኢትዮጵያ መድን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም