የጎሬ-መቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጎሬ-መቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው
መቱ፤ ጥር 22/2018 (ኢዜአ)፡- በኢሉአባቦር ዞን ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ያህያ አዳነ (ኢ/ር) ገለጹ።
ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ የግንባታ ሂደቱ 80 በመቶ መድረሱን እና የአስፓልት ዝርጋታ መጀመሩን አስታውቀዋል።
በቀጣዩ ወር መጨረሻ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለበረራ ክፍት እንዲሆን ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ለኢዜአ አረጋግጠዋል።
የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው መጠናቀቅ የቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማነቃቃት ዕድል ይፈጥራል ያሉት ደግሞ የኢሉአባቦር ዞን ምክትል ዋና አሥተዳዳሪ መሐመድ ጠሃ አባፊጣ ናቸው።
ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የጎሬ-መቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀከት ግንባታ በ2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።