ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር ብሎም በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ የሀገራችንን ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት የመስኖ ስንዴ ምርትን ሳይጨምር 126.69 ሚሊዮን ኩንታል መድረሱን ገልጸዋል።


 

"አርሶ አደሮቻችንን ማድነቅ እና ማመስገን እፈልጋለሁ። ይኽንኑ የሥራ ጽናት ቀጥሉበት" ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም