ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የዩኤስ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የዩኤስ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጽሕፈት ቤታቸው ከተገኙት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የዩኤስ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ቀጣይነት ያለው ትብብር እና መከባበርን አፅንዖት ለሰጠው ደማቅ እና ገንቢ ውይይታቸው ምስጋና አቅርበዋል::