ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ድል ተመልሷል 

አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ተስፋዬ ታምራት በ78ኛው ደቂቃ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል። 

ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ20 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አራተኛ ድሉን አሳክቷል። 


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለስምንተኛ ጊዜ የተሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና በ19 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል። ቡናማዎቹ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፉም።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች መርሐ-ግብሮች ነገሌ አርሲ የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ሸገር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ 17ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም